በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ
በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አለባቸው አሞኜ በቢሮአቸው ውስጥ ተገደሉ።
የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ ” አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ ተገልጋይ በሽጉጥ ተገድለዋል።
ክፍለ ከተማው ስለ ግድያው ተጨማሪ መረጃ ባያደርግም ግድያውን ፈጽማል የተባለለው ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል።
ክፍለከተማው ባወጣው መግለጫ ” አቶ አለባቸው በስራ ቁርጠኝነት የሚታወቁ ናቸው” “በበርካታ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራት አርዓያነት ያለው ስራ የሰሩና ያስተባበሩ አመራራችን ነበሩ ” ሲል ገልጿል።
አመራሩ በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ህክምና ቦታ ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ እንዳልተቻለ ተገልጿል።