ኢትዮ ነጋሪ፣ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም:- ሀገራት ዜጎቻቸውን እያስወጡ ያሉት በጋላባት-መተማ በኩል ነው ተብሏል
ዜጎችን የማስወጣት ስራው በካርቱም ካለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር በመነጋገር ነው
በሱዳ. ያሉ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ
የተለያዩ ሀገራት በሱዳን ያሉ ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ጀምረዋል።
በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ መካከል የተጀመረው ጦርነት ስምንተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል።
ለኢድ በዓል ተብሎ የሶስት ቀን ተኩስ አቁም ቢደረግም ጦርነቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ የተለያዩ ሀገራት በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ትረቶች ላይ ይገኛሉ።
ከካርቱም ዜጎቻቸውን በአየር ትራንስፖርት ለማውጣት ያልተሳካላቸው ሀገራት በየብስ ትራንስፖርት በኢትዮጵያ ድንበር በኩል እያስወጡ መሆኑን ሰምተናል።
ሀገራቱ ዜጎቻቸውን በጋላባት-መተማ በኩል በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በማድረግ ከዚያም ወደ ሀገራቸው እያጓጓዙ ነው ተብሏል።
ሀገራቱ ዜጎቻቸውን ከሱዳን እያስወጡ ያሉት በካርቱም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር በመነጋገር እንደሆነም ተገልጿል።
እስካሁን ሳውዲ አረቢያ 50 የሚሆኑ ዜጎቿን ከሱዳን ያስወጣች ሲሆን ሌሎችም ሀገራት በጥረት ላይ ናቸው ተብሏል።
ሀገራት ዜጎቻቸውን በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በኩል ለማውጣት ቢሞክሩም በስፍራው ከባድ ውጊያ መቀጠሉን ተከትሎ አለመሳካቱ ተገልጿል።
ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን በያዘው የሱዳን ጦርነት እስካሁን ከ415 በላይ ንጹሀን መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጻል።