በአዲስ አበባ በ1 ነጥብ 5 ቢልየን ብር ወጪ የተገነባው “ስቴይ ኢዚ ፕላስ” ሆቴል ወደ ሥራ ሊገባ ነው

በአዲስ አበባ ከአዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ እንጦጦ መስመር ላይ የተገነባው፤ “ስቴይ ኢዚ ፕላስ” ሆቴል ከኹለት ሳምንታት በኋላ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አሚር ሰኢድ እንዳሉት ሆቴሉ በጥንዶቹ ዳግማዊ መኮንን እና ህይወት አየለ ባለቤትነት የተገነባ ሲሆን ሆቴሉ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል ብለዋል፡፡

በአምስት ዓመት ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ታስቦ ግንባታው የተጀመረው ይህ ባለ ስምንት ወለል ህንጻ ኮሮና ቫይራ ተጨምሮበት በስምንት ዓመት ውስጥ መጠናቀቁን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ሆቴሉ በባለ አምሰት ኮከብ ደረጃ መገንባቱን የተናገሩት ደግሞ የሆቴሉ ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሂወት አየለ ናቸው፡፡

እንደ ወይዘሮ ሂወት ገለጻ ሆቴሉ በአጠቃላይ 103 ክፍሎች፣ ከ15 እስከ 1 ሺሕ 500 ሰው ማስተናገድ የሚችሉ 6 የስብስባና የሰርግ አዳራሾች እንዲሁም፤ የኪነ-ጥበብ እና ሌሎች ዝግጅቶችን ማቅረብ የሚያስችሉ ምቹ አዳራሾችም አሉት።

እንዲሁም ሦስት ባር እና አንድ መመገቢያ አዳራሾች ያለውና እራሱን የቻለ የዳቦና የኬክ መጋገሪያ ኪችን ያለው ሲሆን፤ በሰዓት ከ30 ሺሕ በላይ ዳቦ ማምረት የሚችል ማሽን፣ ኦፕን ኪችን እንዲሁም ግዙፍ የላውንደሪ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማሽኖችም ተገጥመውለታል ተብሏል።

ሆቴሉ ከእንጦጦ ፓርክ እና ቦታኒክ ጋርደን ለሚጡ ጉብኚዎች እንዲሁም፤ በእንጦጦ እና ሱልልታ የሩጫ ልምምድ ለሚያደርጉ አትሌቶች በቅርብ የሚገኝ መሆኑን የገለጹት ሃላፊዋ ከአምስት በላይ ለሚሆኑ አትሌቶች ወደ መለማመጃ ስፍራ በነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡም አክለዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *