ኢትዮጵያ ከጦርነት ውድመት ለማገገም 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ

ኢትዮጵያ በጦርነት ከደረሰባት ውድመት ለማገገም 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ

በኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት ህወሀት በሀገር መከላከያ የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር ጦርነት የተነሳው።

በዚህ ጦርነት ምክንያት 800 000 ዜጎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሲገለጽ የግለሰቦች እና የመንግስት መሰረተ ልማቶች ወድመዋል።

ጦርነቱ አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ጦርነቱ ቆሟል።

ይህ ለሁለት ዓመት የዘለቀው ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች ሀብቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የፋይናንስ ሚንስቴር ገልጿል።

ጦርነቱ ክፉኛ የጎዳቸው ትግራይ ፣አማራ እና አፋር ክልሎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋልም ተብሏል።

ይህ የመልሶ ግንባታ በጀት ከፌደራል መንግሥት ፣ ዓለም ባንክ እና ከምዕራባዊያን ሀገራት በሚገኝ እርዳታ ለመሸፈን መታቀዱም ተገልጿል።

የፌደራል መንግሥት እና ህወሀት የሰላም ስምምነቱን በመተግበር ላይ ሲሆኑ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር በመቋቋም ላይ ይገኛል።

የህወሀት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ከቀናት በፊት ወደ አዲስ አበባ መጥተው በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም እና በዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *