08
Oct
አሜሪካ ባወጣችው አዲስ መግለጫ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ እንደሚችል አስጠንቅቋል። አሜሪካ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ በጥቅምት ወር በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች እንደደረሷት ገልጻለች። አሜሪካ አክላም ዜጎቿ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ባለሥልጣናት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስባለች። አሜሪካ ማምሻውን ባወጣችው የደህንነት ማስጠንቀቂያ በተጨማሪም ዜጎቿ በማንኛውም ምክንያት ወደ አማራ ክልል ላሊበላን ጨምሮ፣ ወደ ትግራይ ክልል ወይም ወደ ዓፋር ክልል ከማንኛውም ዓይነት ጉዞ እንዲቆጠቡ አሳስባለች። ቀደም ሲል በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎቿ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከሆነ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ፣ ካልሆነ ደግሞ ሁኔታዎች እስኪሻሻሉ ድረስ ባሉበት ቦታ እንዲጠለሉ አሳስባለች። የአሜሪካ ዜጎች ራሳቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁ…