07
Nov
በአዲስ አበባ ከተማ ከ1997 እስከ 2007 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ተገንብተው ለአገልግሎት በበቁ የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ሕንፃዎች ላይ የተስተዋሉ የግንባታ ጥራት ጉድለቶችን በሙያዊ አሰራር ለማስተካከል የሚያስችል ሥራ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል። ኮርፖሬሽኑ እንደገለጸው በአስርቱ ዓመታት ውስጥ በተገነቡት ሕንፃዎች ላይ የተከሰቱትን ችግሮች ዓይነትና የጉዳት ደረጃ በጥናት ለመለየት ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሰፊ ሳይንሳዊ ምርምር ተካሂዷል። በተካሄደው ጥናት መሠረት ቅድሚያ የጥገናና የማስተካከያ እርምጃ የሚያስፈልጋቸው ሕንፃዎች የተለዩ ሲሆን በነዋሪዎች ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ሳይደርስ እርምቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል። ኮርፖሬሽኑ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግና አስፈላጊዎቹን የሥራ ተቋራጮች በመመደብ ሥራውን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጥራት…