02
Feb
አየር መንገዱ እንደገለጸው ባለፈው ሃሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ሁለቱ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል። በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ የገለጸው አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሎሜ (ቶጎ) መቀመጫውን ካደረገው አስካይ አየር መንገድ ጋር የ40% የባለቤትነት ድርሻና የቴክኒክ አጋርነት አለው። የአስካይ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ኢላማ…