11
May
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደገለፀው ይህ ዘመናዊ ሎተሪ ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ በዲጅታል መላ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብሏል። በዲጂታል ሎተሪ ለረጅም ዓመታት በመፋቅ እድለኛ የሚያደርጉት የፈጣን እና የቢንጎ ሎተሪዎችም በዲጅታል መንገድ እንደተካተቱ ተገልጿል።ከሀምሳ ሚሊዮን ብር ሽልማት አንስቶ በርካታ የጨዋታ አማራጮችን የቀረበበት ሲሆን በስምንት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ይህንን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል። አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዲጅታል ሎተሪ በተጨማሪ በሃምሳ ሺህ ብር ሽልማት የከፈተውን የእድል በር ወደ ሃምሣ ሚሊየን ብር ከፍ ለማድረግ እንደበቃም ተናግሯል። ብሔራዊ ሎተሪ በየጊዜው አዳዲስ የሎተሪ እድኮችን ለደንበኞቹ ያስተዋወቀ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት አድማስ…