Militarydeal

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ62 ዓመታት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ታሪካዊ የሚባል ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋትም የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑም ተገልጿል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ፈርመዋል። ስምምነቱ ከሃገራቱ በተጨማሪ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት የጎላ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ተናግረዋል። በቀጣይም ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ የኬንያ መከላከያ በቁርጠኝነት ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ መናገራቸውንም ከኢኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ኢትዮጵያና…
Read More