12
Mar
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው የፌደራል መንግስትን እገዛ የጠየቀው። ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው “ከጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አንዳንድ የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ከተልኮ ወጭ የአንድ ጠባብ ቡድን የስልጣን ጥም ለማርካት በማለት ግልፅ የመፈንቅለ መንግስት እንስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል” ብሏል። “በዚህ ሳምንትም በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ግንባር አዛዦች እንቅስቃሴው በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል” ብሏል መግለጫው። ይህንን አደገኛ እንቅስቃሴ ለመግታት እና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሁሉ ለማስቆም የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለትግራይ ጦር ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ትእዛዝ ቢሰጥም ማስቆም እንዳልቻለ አስታውቋል። ሁኔታው እልባት ባለማግኘቱ የግንባሩ የጦር አዛዦች እገዳ እንደተጣለባቸው ያመላከተው መግለጫው፤ የጸጥታ ቢሮ…