27
Jun
ግለሰቡ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማን በመጎብኘት ላይ እያለ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡ የ55 ዓመት እድሜ እንዳለው የተገለጸው ይህ ሩሲያዊ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሀይቅ ላይ በመዋኘት ላይ እያሉ ህይወቱ አልፏል ተብሏል፡፡ በቢሾፍቱ ኩርፊቱ ሀይቅ በመዝናናት ላይ ከነበሩት የዉጭ ሀገር ዜጎች መካከል አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለዉ የ 55 ዓመት ህይወቱ ማለፉን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት ግለሰቡን ለሞት ያበቃዉ በኩሪፍቱ ሀይቅ 150 ሜትር ጥልቀት ባለው ኩሪፍቱ ሀይቅ ዘልቆ በመዋኘት ላይ ሳለ ህይወቱ ማለፉን ተገልጿል፡፡ ግለሰቡ ባሳለፍነው እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ለመዋኘት ወደ ሀይቁ ውስጠኛው ክፍል ከገባ በኋላ ሳይመለስ ቀርቷል…