Gode

በሶማሊ ክልል ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ተጀመረ

በሶማሊ ክልል ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ተጀመረ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የዩሪያ ማዳበሪያ እና ጌዴ ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን አስጀምረዋል። የዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ይገነባል ተብሏል። ጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ ደግሞ የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል። የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለውም ተብሏል። በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል። ከአንድ ወር በፊት አሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ…
Read More