17
Feb
አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬታማ እንዲሆን የአመራርነት ሚናቸውን ካሳረፉ ሰዎች መካከል ዋነኛው ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከለቀቁ በኋላ ወደ ኪጋሊ አምርተው የሩዋንዳ አየር መንገድን በማቋቋም አሁን ላይ በማደግ ላይ ካሉ የአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ሆኗል። ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ኡጋንዳ ኢትዮጵያዊውን የአቪዬሽን መሪ የሆኑት አቶ ግርማ ዋቄን ቀጥራለች። አቶ ግርማ የኡጋንዳ አየር መንገድን በጊዜያዊነት ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙ ሲሆን በተጨማሪም የሀገሪቱን አቪዬሽን አማካሪ ሆነውም እንደሚያገለግሉ የትራንስፖርት ሚንስቴር ገልጿል። የኡጋንዳ አየር መንገድ በ1985 ዓ .ም የተቋቋመ ቢሆንም በኪሳራ ምክንያት በ2009 ተዘግቶ ነበር። ከስድስት ዓመታት በፊት ዳግም የተቋቋመው የኡጋንዳ አየር መንገድ በኪሳራ ላይ ካሉ የአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነበር።…