09
Mar
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስድስት አዳዲስ የጭነት መርከቦችን ግዢ ሊፈፀም እንደሆነ አስታውቋል። 62 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት አልትራማክስ የደረቅ ብትን ጭነት መርከቦች በአጭር ግዜ ተገዝተው አገልግሎት እንደሚጀምሩ ድርጅቱ ገልጿል፡፡ የቀሪ አራት መርከቦች ግዥ በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ መርከቦቹን የምትገዛው የሀገሪቱን የገቢ ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ያግዛሉ በሚል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ 10 መርከቦች እንዳሏት ይነገራል። ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ መረከቧ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ባህር ዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት መርከቦች ለኪሳራ ዳርገውኛል በሚል መሸጡ ይታወሳል። በተሸጡት ሁለት መርከቦች…