Ethiopianinsaudiarabia

ሁለት ኢትዮጵያዊያን በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያውያን አንድ ህንዳዊ በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል። የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት በቅርቡ በጂዳ ከተማ 'አንድ ህንዳዊ ዜጋ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለዋል' ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ የጂዳ ግዛት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ደንቦች በመጣስ በሕገ-ወጥ መንገድ በሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል። በከተማዋ አቅራቢያ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ሕገ-ወጥ ዕፅ በመገበያያት ላይ በነበሩ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ጠብና አለመግባባት ሳቢያ ህንዳዊው ግለሰብ በጥይት መመታቱን ገልፍ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በዚህም በግጭቱ ወቅት ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ ኢትዮጵያዊ በህንዳዊው ተጎጂ ላይ ተኩስ ከፍቶ ጉዳት እንዳደረሰበት የገለጸው ፖሊስ፤ በጥይት የተመታው ግለሰብ ወዲያውኑ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ቢወሰድም፣…
Read More