14
Jul
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የከፍተኛ ትምህርት ማስረጃ አሰጣጥንና የደረጃ ግምገማ ሂደትን ለማሻሻል ያስችላል የተባለውን አዲስ ረቂቅ መመሪያ ለህዝብ አስተያየት ክፍት አድርጓል። ባለስልጣኑ "የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ ቁጥር 990/2016" ላይ ማሻሻያ ለማድረግ በተዘጋጀው በዚህ ረቂቅ ላይ የትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ጥሪ አቅርቧል። ተቋሙ እንዳስታወቀው ይህ መመሪያ ያስፈለገው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የትምህርት ማስረጃዎችን የማረጋገጥ ሂደት ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ ለማድረግ በሚል ነው። በተለይም በደረጃ ግምገማ እና በማስረጃ ማረጋገጫ ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ታልሞ መዘጋጀቱም ተገልጿል። ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የመንግስትም ሆነ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተምረው ከ2010 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለተመረቁ…