25
Aug
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ወቅት፣ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ክምችት ማሰባሰቡን ይፋ አድርጓል። ይህ ባንኩ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አበድሮ የነበረውን ገንዘብ ከባለዕዳዎች መልሶ የሰበሰበው መጠን አፈጻጸም ከታለመለት ግብ በ5 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ51.6 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል። የባንኩ ዋና ትኩረት ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና እና ለሌሎች ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዚሁ በጀት ዓመት 18.0 ቢሊዮን ብር ገቢ በማሰባሰብ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና፣ ማዕድን ማውጣት፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ኢንቨስትመንቶች የገንዘብ አቅርቦት የሚያመቻች መንግስታዊ ተቋም…