12
Feb
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ አለኋት ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነበር ኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች መውጫ ስፍራ በአለት የተደፈነባቸው፡፡ በማህበር ተደራጅተው ኦፓል እንዲያወጡ የተደራጁት እነዚህ ወጣቶች ቁጥራቸው 20 ሲሆን ከመሩት በህይወት ለማትረፍ የአካባቢው ማህበረሰብ ሌት ተቀን በፈረቃ እየቆፈረ መሆኑን የዞኑ መንግስት ኮሙንኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ እያሱ ለአልዐይን ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ እያሱ ገለጻ ከሆነ ወጣቶቹ ሌሊት ላይ ማዕድኑን ለማውጣት እየቆፈሩ እያሉ መውጫቸው በዓለት የተዘጋ ሲሆን በአካባቢው የነበሩ በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡ ጥር 30 ቀን የተከሰተው ይህ አደጋ ከመሬት ውስጥ ባለው ዋሻ ውስጥ ያሉትን ወጣቶች የደላንታ ወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዘመቻ…