11
Dec
የቀድሞው የአደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል። የፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ፣ አቶ ምትኩ ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር በመሆን የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴን ጨምሮ በርካታ የምግብ እርዳታ ቁሳቁሶችን ከመጋዘን በማውጣት ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ አስረድቷል። በተጨማሪም፣ ከ472 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲከፈል በማድረግ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ…