Akobomining

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ፡፡ የፈንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በኢትዮጵያ የወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ ከተሠማራው የኖርዌው አኮቦ የማዕድን ኩባንያ  ሦስት ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 7.4 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ታዬ፤ “በአኮቦ ማዕድን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መስፋፋት ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ እመርታ ነው” ብለዋል፡፡ ውሳኔው ኢትዮጵያ ከክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ የአክስዮን ገበያ እንድትመለስ ያደረገና ለቀጣይ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንቶች በር የከፈተ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢንቨስትመንቱ አኮቦ አዲስ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የሚደግፍ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን ወርሃዊ የወርቅ…
Read More