Airport

የክልል አየር ማረፊያዎች ዓለም አቀፍ በረራዎች ማስተናገድ ሊጀምሩ ነው

የክልል አየር ማረፊያዎች ዓለም አቀፍ በረራዎች ማስተናገድ ሊጀምሩ ነው

ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በተጨማሪ በሌሎች የክልል አየር ማረፊያዎች ማስተናገድ ሊጀመር መሆኑን የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል። ባለስልጣኑ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ አበራ፣ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እና የግል አየር ትራንስፖርት ኦፕሬተር ተወካዮች በተገኙበት፤ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የባለድሻ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በባለስልጣኑ የአየር ትራንስፖርትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አማካሪ አቶ እንደሻው ይገዙ ባቀረቡት ሪፖርት፤ በ2018 ዓ.ም ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በተጨማሪ በሌሎች የሀገሪቱ ክልል ኤርፖርቶች ማስተናገድ እንደሚጀመር ተናግረዋል። "የክልል ኤርፖርቶችን ማስተሳሰር የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጨምር እንዲሁም የደንበኛውን እንግልት መቀነስ የሚያስችል ነው" ያሉት አቶ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አምስት ተጨማሪ የአገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ። አሁን ላይ አየር መንገዱ 136 ዓለም አቀፍ እንዲሁም 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሉት የጠቆሙት ስራ አስፈጻሚው ተጨማሪ የአገር ውስጥ መዳረሻዎችን ለማስፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አምስት የአገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል።  ኤርፖርቶቹ የሚገነቡት በሚዛን ቴፒ አማን፣ ያቤሎ፣ ጎሬ፣ መቱና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውን ገልጸው፤ አራቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል። ይህም በአገር ውስጥ ያሉ ደንበኞች ፍላጎት ተከትሎ የሚተገበር መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ሌሎች መዳረሻዎችን ጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ ግንባታቸው እንደሚቀጥል ተገልጿል። በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት…
Read More