ADB

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ104 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ104 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያግዝ የ104 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ማጽደቁን ገልጿል። የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ያጸደቀው የገንዘብ ድጋፍ 52 ሚሊዮን ዶላሩ ከአፍሪካ ልማት ፈንድ የተገኘ መሆኑም ተመላክቷል። ቀሪው የገንዘብ ድጋፍ ደግሞ የባንኩ የብድር አጋር ከሆነው በኮሪያ-አፍሪካ የኢነርጂ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ስምምነት ከኮሪያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል። የባንኩ የኃይል ሥርዓት ልማት ዳይሬክተር ባቺ ባልዴህ፤ ፕሮጀክቱ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ያለውን የኃይል ቋት አቅም በማሳደግ ታዳሽና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል። መንግሥት በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚያደርጋቸውን የኃይል አቅርቦት ጥረቶች የሚያግዝ ሲሆን፤ አርብቶ አደሮች፣ አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ 157 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ…
Read More