06
Nov
"የአንድ ግጥም አንድ ወግ" ኪነ ጥበባዊ ዝግጅት በድምቀት የተከናወነ ሲሆን በዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተወዳጅ ድራማዎችን እያቀረቡ ያሉት ተዋናዮችና ፕሮዲዩሰሮች የዝግጅቱ ልዩ እንግዶች በመሆን ልምዳቸውን አካፍለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ " በሀገራችን የኪነ ጥበብና በተለይም በቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ስራዎች ጉልህ አበርክቶ እያከናወነ ካለው ዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን ጋር በትብብር የጥበብ መድረክ ማዘጋጀታችን ወደፊትም ይቀጥላል። ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋርም በትብብር ለመስራት ባሕል ማዕከላችን ክፍት ነው" ሲሉ በመክፈቻ ዝግጅቱ ወቅት ተናግረዋል። የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ኃላፊ ወ/ሮ ትህትና ተስፋዬ በበኩላቸው " እኔ እና ዲኤስቲቪ" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የብራንድ ትውውቅ ከ አአዩ ባሕል ማዕከል ጋር መዘጋጀቱን ገልፀው አብዛኛው…