05
Jan
በቮልስ ዋገን አይዲ ሲሪየስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱ ተገልጿል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ቮልስ ዋገን አይዲ ሲሪየስ (ID Series) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ ጥላ ነበር፡፡ ከቻይና ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የነበረው የጀርመን ምርት የሆነው ቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ ባትሪው ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጋር የሚጣጣም አይደለም በሚል በቀረበው ቅሬታ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታግዶ ቆይቷል፡፡ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪና ተሽከርካሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አበራ ሞሲሳ እንዳሉት፤ የጀርመን መንግሥት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ መሠረት ቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ እንዳይገባ ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ደብዳቤው የተሽከርካሪዎች ባትሪ ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጋር የማይጣጣም…