05
Oct
ፕሬዝዳንቷ በX ወይም በቀድሞው ትዊተር ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሁፍ ላይ "ዝምታ ነው መልሴ" የሚል ጽሁፍ አጋርተዋል። ለምን ዝም እንዳሉ በጽሁፋቸው ላይ ያልገለጹት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ " እነ ጥላሁን ገሰሰ፣ ቴዲ አፍሮ፣ አሊ ቢራ ፣ማህሙድ አክመድ ... ድንቅ ድምጻዊያን መካከል ናቸው። ሲሉም አክለዋል። ፕሬዝዳንቷ የማህሙድ አህመድ ዘፈንን በሚያስታውሰው "የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው" የሚለውን ግጥምም በጽሁፋቸው ላይ ጠቅሰው አጋርተዋል። ዝምታን "ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ምን ደርሶባቸው እንደከፋቸው፣ ለምን እንደከፋቸው እና ለምን ዝም እንዳሉ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በበኩሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ያጋሩት ጽሁፍ የግላቸው እንጂ የጽህፈት ቤቱ እንዳልሆነ ጠቅሷል። ኢትዮ…