በዓለማችን ካሉ ስመ ጥር የጤና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የቱርኩ አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ ቢሮውን ከፍቷል።
ይህ ቢሮ የኢትዮጵያ ታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው በቱርክ ስለሚገኙ ልዩ የህክምና አገልግሎቶች እና የህክምና አማራጮች መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በሀገር ቤት ሆነው ከሀኪሞች ጋር በቀጥታ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎትን ይሰጣል።
አዲሱ አጂባደም ኸልዝ ፖይንት አዲስ አበባ ሆስፒታሉ በዓለም ዙሪያ ከከፈታቸው የመረጃ ማዕከሎች 52ኛው ሲሆን ማዕከሉ፤ የታካሚዎችን ነባር የህክምና መረጃዎችን ግምገማ ከማከናወን እና ተጨማሪ የባለሙያ ምክር ከመስጠት ጀምሮ እስከ ህክምና ዕቅድ ዝግጅት፣ የጉዞ ዝግጅት ማስተባበር እና ከህክምና በኋላ የሚደረግ ክትትል ድረስ ባሉት ሂደቶች ሁሉ ለታካሚዎች ድጋፍ ይሰጣል ተብሏል።
አጂባደምን ለኢትዮጵያዊያን ታካሚዎች ይበልጥ ማቅረብ ቢሮው በአዲስ አበባ ቦሌ ብራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ሴንቸሪ ህንፃ ውስጥ ይገኛል።
ማዕከሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ታካሚዎችን ከአጂባደም ሆስፒታሎች እና በቱርክ ከሚገኙ የህክምና ቡድኖች ጋር ያገናኛል።
ከአገልግሎቶቹ መካከልም ተጨማሪ የህክምና አስተያየቶችን መስጠት፣ የህክምና ቪዛ ማመልከቻዎች በተገቢው መልኩ እንዲከናወኑ መደገፍ፣ የጉዞ እና የሎጂስቲክስ ጉዳዮችን ማስተባበር እና ከህክምና በኋላ በሚደረግ ክትትል ላይ የሚደረግ ድጋፍን ያካትታሉ። ታካሚዎች የህክምና መረጃዎችን ስለማቅረብ፣ የህክምና ሁኔታ ግምገማዎችን ስለማግኘት እና ከተገቢ ሀኪሞች እና ሆስፒታሎች ጋር ቀጠሮዎችን ስለማስተባበር መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው በአዲስ አበባ በአካል ከሚያገኟቸው ባለሙያዎች በአፍመፍቻ ቋንቋቸው እየተግባቡ የጉዞ ዝግጅቶችን ከማድረጋቸው በፊት ስለታቀዱት የህክምና ዕቅዶች፣ ስለሚገመቱ ወጪዎች እና ስለሚጠበቁ የጊዜ ሰሌዳዎች መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ይህም ህክምና ፈላጊዎች በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ እና ህክምናን በከፍተኛ በራስ መተማመን ወደ ውጭ አገር እንዲሄዱ ይረዳቸዋል።
ሆስፒታሉ ከሚሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች መካከል ኒውሮሎጂ እና ኒውሮሰርጀሪ ለአዋቂዎችና ለህጻናት ውስብስብ የነርቭ እና የነርቭ ቀዶ ጥገና የሚያሻቸው ህመሞች የምርመራና የቀዶ ጥገና አገልግሎት፣ እንዲሁም የስልጠና እና የፌሎውሺፕ እድሎች፣ ኩላሊት እና ጉበት ንቅለ ተከላ ለአዋቂዎችና ለህጻናት አጠቃላይ የትራንስፕላንት (የአካል ክፍሎች ንቅለ-ተከላ) አገልግሎት፤ ይህም ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ከሚሰጡት ወቅታዊ የጤና ሁኔታ ግምገማ እና ከቀዶ ጥገና ጀምሮ እስከ ረጅም ጊዜ ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት ያካትታል።
የሜዲካል እና ራዲዬሽን ኦንኮሎጂ
የሜዲካል እና የጨረር ኦንኮሎጂን ከቀዶ ጥገና፣ ከምርመራ እና ከሌሎች የህክምና ዘርፎች ጋር በማጣመርም እንደሚሰጥም ተገልጿል።
በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ታካሚ በተለየ ሁኔታ ታቅዶ የሚከናወን የካንሰር ህክምና።
በተፈጥሮ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ጥንዶች የጽንስ እና የማህፀን ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥም ተነግሯል።
አጂባደም በየዓመቱ ከ50,000 በላይ ዓለም አቀፍ ታካሚዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ከ600 በላይ ዓለም አቀፍ የታካሚ አገልግሎት ሰራተኞች ከህክምናው በፊት፣ በህክምና ጊዜ እና በኋላም የሕክምና ሂደት ማስተባበር፣ የቋንቋ ትርጉም እና የሎጂስቲክስ ድጋፍ ይሰጣል።