የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴት ፓይለቶች ቁጥር 95 መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በማስመልከት፣ በሴቶች ባለሙያዎች ብቻ የሚመሩ 8 በረራዎችን በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ተለያዩ የአለም ሀገራትና የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንደሚያከናውን ገልጿል።

አየር መንገዱ ዕለቱን በማስመልከት ባከናወነው መርሃግብር ላይ እንደገለጸው ወደ ካይሮ፣ ጅቡቲ፣ ናይሮቢ፣ ፍራንክፈርት፣አክራ፣ ሙምባይ፣ ዊንድሆክ እና ድሬዳዋ የሚደረጉ በረራዎች ሙሉ በሙሉ በሴት ፓይለቶች፣ ቴክኒሻኖች እና የበረራ አስተናጋጆች የሚመሩ ይሆናሉ ተብሏል።

ይህ ልዩ የበረራ መርሃ ግብር ሴቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያላቸውን አቅምና ተሳትፎ ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ካሉ ጠቅላላ ሰራተኞች መካከል 40 በመቶ ያህሉ ሴቶች ሲሆኑ፣ 35 በመቶ የሚሆነውን የአመራር ቦታ የያዙትም ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

በተለይም ቀደም ሲል ለወንዶች ብቻ የተከለሉ ተደርገው ይታሰቡ በነበሩ የቴክኒክ ዘርፎች ላይ የሴቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቅሷል።

በአሁኑ ወቅት የአየር መንገዱ የሴት ፓይለቶች ቁጥር 95 መድረሱንም በዝግጅቱ ላይ አቶ መስፍን ጣሰው ጠቅሰዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል-ኢራን ጦርነት ምክንያት በሳምንት የ137 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እያስተናገደ መሆኑን ገልጿል።

ከሰባት ቀናት በፊት የተጀመረው የእስራኤል-ኢራን ጦርነት ጉዳቱ በመላው ዓለም ላይ ሲሆን ኢትዮጵያም የጦርነቱ ተጎጂ መሆኗ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀው በዚህ ጦርነት ምክንያት በየሳምንቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የካርጎ በረራን ሳይጨምር የመንገደኞችን ብቻ 101 በላይ በረራዎችን እየሰረዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በረራዎቹ በመሰረዛቸው ምክንያትም እስከ 137 ሚሊዮን ዶላር በማጣት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *