ያንጎ ኢትዮጵያ፣ የመንገድ ደኅንነት ሥልጠና እና የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና መስጠት ጀመረ
የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነውና በጂቱጂ አይቲ ሶሊውሽን አ.ማ. እና በኤለጋንስ ኢምፖርት ኤንድ ኤክስፖርት ፒኤልሲ ሥር የሚተዳደረው ያንጎ ኢትዮጵያ፣ ለደኅንነት፣ ለአገልግሎት ልህቀት እና ቅልጥፍና እንዲሁም ለማኅበረሰብ ተሳትፎ ያለውንቁርጠኝነት በማጠናከር የመንገድ ደኅንነት ፕሮግራም እና የመጀመሪያ እርዳታ እና የአገልግሎት ልህቀት ሥልጠና መርሐግብር ለአጋር አሽከርካሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡
“ያንጎ ኬርስ” በተሰኘው የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ስር የተጀመረው ይህ ተነሣሽነት፣ የኩባንያው ትኩረት ይበልጥ ደኅንነታቸው በተጠበቁ መንገዶች፣ በጠንካራ ማኅበረሰቦች እናለተሳፋሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡
የሥልጠናው ክፍለ ጊዜ፣ አጋር አሽከርካሪዎች የመንገድ ደኅንነት ግንዛቤ እና ተግባራዊ የመጀመሪያ ህክምና ክህሎቶችን እንዲታጠቁ በማድረግና የተሳፋሪዎችን ልምድ በማጎልበት- በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፊው ሕዝባዊ ደኅንነት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
በተመሳሳይ ጊዜም፣ ያንጎ ከፍተኛ አፈጻጸም፣ ቁርጠኝነት፣ አስተማማኝነት ላላቸው እና ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት ለሚሰጡ አጋር አሽከርካሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል።
ኩባንያው ለእነዚህ ግለሰቦችእውቅና በመስጠት፣ አሽከርካሪዎች በዘርፉ ለሚጫወቱትወሳኝ ሚና አፅንዖት በመስጠት ለሥራቸው ያለውን አድናቆትያሳያል።
በፕሮግራሙ ላይ፣ በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ የሆኑት ይቅናአለም አበበ (ዶ/ር) “የያንጎን አገልግሎት የሚጠቀሙና የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የልብ ትርታዎቻችን ናቸው ብለዋል፡፡
ሃለፊው አክለውም “ደኅንነታቸው እና ዕድገታቸው ቀዳሚ ጉዳዮቻችን ናቸው። በተለይ በዚህ ራስን የማደስ ጊዜ፣ በሥልጠና፣ ዕውቅና በመስጠት እና የማኅበረሰብ ተነሳሽነት ላይ ኢንቨስት በማድረግ ለሾፌሮቻችን ብቻ ሳይሆን ለምናገለግላቸው ማኅበረሰቦች ደኅንነት ተቆርቋሪነታችንን በማሳየት የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ላይ የድርሻችንን እንደምናበረክት እናምናለን።” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፕሮግራሙ፣ ጥልቅ የሆነ የባህል ትሥሥር፣ ራስን በዕውቀት የማደስ እና የደኅንነት እሴቶችን፣ ከእውቅና እና የግላዊ የዐቅም መሻሻሎች ጋር የማገናኘት ርዕይን የሰነቀ ነው ተብሏል።
ይህ በግላዊ በጎፈቃድ እና መነሣሣት ላይ የተመሠረተ መርሐ ግብር፣ ያንጎ ከሰፊው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጋር ያለውን ትሥሥር እንደሚያጠናክር ታምኖበታል፡፡
ያንጎ፣ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ባለው የግል ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ ውስጥ የመሪነት ቦታውን እያጠናከረ ገኛል።
ያንጎ፣ ተጨማሪ አሽከርካሪዎች በማደግ ላይ ያለው የያንጎ ትራንስፖርት አገልግሎት ሥርዓት አካል እንዲሆኑ ጥሪውን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ይህም የሥልጠና ዕድሎች ማግኘትን፣ የዕውቅና ፕሮግራሞችን እና የአሽከርካሪዎችን አስተዋጽዖ ዋጋ የሚሰጥ ደጋፊ የግንኙነት መረብን ጨምሮ በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አካቷል።
ያንጎ ግሩፕ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱን በዱባይ ያደረገ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 በላይ በሆኑ የዓለማችን ሀገራት አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡