በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለት የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ተገደሉ

የክልሉ ኮሙንኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኦሞ ሱሪ ወረዳ በጉብኝት ላይ የነበሩ ሁለት የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል።

የተገደሉት ሰዎች ሁለቱ የቱርክ ዜግነት አላቸው የተባለ ሲሆን ሾፌራቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ተገልጿል።

ግድያው ትናንት ጠዋት 2:20 ላይ እንደተፈጸመ የተገለጸ ሲሆን የገዳዮቹ ማንነት የአርብቶ አደር ሽፍቶች መሆናቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

ገዳዮቹን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የክልሉ ጸጥታ ሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምሯልም ተብሏል።

ሽፍቶቹ ግድያውን የፈጸሙት ለዝርፊያ በሚል እንደሆነም የክልሉ ኮሙንኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል።

በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዳያደርጉ የጉዞ እገዳ እና ማስጠንቀቂያዎችን ማውጣታቸው ይታወሳል።

ለአብነትም ካናዳ እና ብሪታንያ ከወራት በፊት ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አልያም ከተጓዙ በሚል ልዩ ጥንቃቄ የሚያደርጉባቸውን እንዲሁም በፍጹም እንዳይጓዙ በሚል ማስጠንቀቂያዎችን ማውጣታቸው ይታወሳል።

የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በአንጻራዊነት የተሻለ ደህንነት ያለባቸው አካባቢዎች ሆነው ቆይተዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *