የአለምዓቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ራይድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግለው መተግበሪያው ውስጥ የሚገኘውን የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ አሻሽያለሁ ብሏል።
ተሻሻለው መተግበርያ እያንዳንዱ ተጓዥ ዝርዝር የደህንነት መስፈርቶች መሟላታቸውን የሚያረጋግጥበት አገግሎግሎት፥ በወቅታዊ የጉዞ ሁኔታ መረጃ ላይ ተመስርቶ ምን አይነት የደህንነት እርምጃዎች መወሰድ እንደሚገቡ መረጃ የሚሰጥ እንዲሁም ስለ ጉዞ ደህንነት አጠቃላይ የደህንነት መረጃዎች የሚሰጥ የማዕከል አገልግሎት የተካተተበት ነው ተብሏል።
አዲሱ የደህንነት ማዕከል የመተግበሪያውን አጠቃቀም ማንበብ፣ የግል መረጃን መሙላት ፣ የሚያምኗቸውን ሰዎች ስልክ ቁጥር መሙላት፣ የራስን ፎቶ ማንሳት እና ኢ-ሜል መቀየርን የመሳሰሉ ተሳፋሪዎች መሙላት ያለባቸውን ዝርዝሮችም ይይዛል።
ከዝርዝሩ ውስጥ የጎደለ ነገር ካለ መተግበሪያው ያልተሞላው ላይ ምልክት በማድረግ ተሳፋሪው እንዲሞላው ይጠይቃል።
ተሳፋሪዎች የአጋር አሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ፣ አደጋ ከተፈጠረ እንዴት እርዳታ መጠየቅ እንደሚችሉ እና የእያንዳንዱ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ መረጃን አንድ ቦታ ላይ ያገኛሉ።
የመተግበሪያው ዋና ገፅ ላይ በፍጥነት የእርዳታ ጥሪ ማድረግ የሚያስችሉ ቁልፎች ይገኛሉ።
“ዋናው ትኩረታችን ደህንነት ነው ፣ ጠንካራ የደህንነት እርምጃዎችን መተግበር እና የደህንነት ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ተጠቃሚ እንዲታዩ እና ግልጽ እንዲሆኑ ማድረግም አስፈላጊ ነው ብሎ እንደሚያምን ኩባንያው በላከልን መግለጫ ላይ ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ የቀናለም አበበ
(ዶር) እንዳሉት አዲሱ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ ተሳፋሪዎች መኪናውን ከጠሩበት ሰዓት ጀምሮ ጉዞው እስኪጠናቀቅ ድረስ በእያንዳንዱ የጉዞ ደረጃ ላይ የእነሱን ደህንነት ለመጠበቅ ምን እየሰራን እንደሆነ በትክክል ማየት ይቻላል ብለዋል።
አዲሱ የደህንነት ማዕከል ጉዞው ያለበትን ሁኔታ እና የትኞቹ የደህንነት እርምጃዎች እንደተወሰዱ ያሳያል ያሉት ሀላፊው ለደህንነት ቁጥጥር እና ለአነዳድ ቁጥጥር ልዩ ትኩረት መስጠቱንም ተናግረዋል ።
በአጋር አሽከርካሪ ስማርት ስልኮች ውስጥ ካለው የፍጥነት መለኪያ እና ጋይሮስኮፖች መረጃን በመቀበል በፍጥነት መጨመር ፣በፍጥነት መቀነስ እና በማሽከርከር ላይ የሚፈጠሩ ለውጦች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ከእያንዳንዱ ደህንነቱ ካተጠበቀ ማሽከርከር በኋላ ለአሽከርካሪው የበለጠ በጥንቃቄ እንዲነዳ የሚያስጠነቅቅ መልዕክት ይላካል የተባለ ሲሆን አጋር አሽከርካሪው ማስጠንቀቂያውን ችላ ካለ ለስራ ያለው እድል ሊገደብ ይችላል።
የያንጎ ራይድ አገልግሎት አንዱ ዋናው ትኩረት ደህንነት ሲሆን አጋር አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ከጉዟቸው በፊት እና በኋላ እና በጉዟቸው ላይ ሆነው የሚገለገሉባቸው ከ25 በላይ ልዩ የሆኑ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያዎች መቅረባቸው ተገልጿል።
እነዚህም የፍጥነት እና የአነዳድ ቁጥጥር ፣ የሚጓዙበትን መንገድ እና የጉዞ መረጃውን ለሚያምኑት ሰው ማጋራት መቻል፣ በአደጋ ጊዜ በፍጥነት ጥሪ ማድረጊያ መንገድ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ።
ያንጎ ግሩፕ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ቴክኖሎጂዎችን የአካባቢው ማህበረሰብ ወደ ሚጠቀምባቸው ዕለታዊ አገልግሎቶች በመቀየር ላይ ይገኛል።
ያንጎ ቡድን በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በደቡብ እስያ እና በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ከ30 በላይ አገሮች ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የዴሊቨሪ አገልግሎት፣ ፉድቴክ እና መዝናኛን ጨምሮ የተለያዩ የዲጂታል አገልግሎቶቹን በማቀረብ ላይ ነው።