የአውስትራሊያው የማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

ዋና መቀመጫውን ፐርዝ አውስትራሊያ ያደረገው ግዙፍ የማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ውስጥ አዲስ የኢንቨስትመንት ውል ፈጽሟል።

አስካሪ ሜታልስ የተባለ የማዕድን አሳሽ ኩባንያ በአፍሪካ ያለውን የፍለጋ እንቅስቃሴውን ወደ ኢትዮጵያ በማስፋፋት ሪፍት ቫሊ ሜታልስ የተባለውን የግል ኩባንያ ሙሉ በሙሉ ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሱን በይፋ አስታውቋል።

ሪፍት ቫሊ ሜታልስ በደቡባዊ ኢትዮጵያ በሚገኘው በአዶላ አካባቢ አምስት ትላልቅ የወርቅ ፕሮጀክቶች ባለቤት ሲሆን፣ ይህ ስምምነት አስካሪ ሜታልስ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን ሳካሮ፣ ሳካሮ ምዕራብ፣ ሌጋ ደምቢ ደቡብ፣ ሜጋዶ እና ዋዩ ቦዳ የተባሉትን 460 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ፕሮጀክቶች እንዲያገኝ አስችሎታል።

ይህ ስምምነት አስካሪ ሜታልስ ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅና የመዳብ ክምችት በሚገኝበት ክልል ውስጥ ስልታዊ የሆነ ቀዳሚ ተሳትፎ እንዲያደርግ እንደሚያስችለው ተገልጿል።

ስምምነቱ የመጀመሪያ ክፍያ 200,000 ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና 200,000 ዶላር በአስካሪ የአክሲዮን ድርሻ እንዲሁም የፍለጋው ውጤት በሚታይበት ደረጃ የሚከፈል ተጨማሪ ክፍያዎችን እንደሚያካትት ተገልጿል።

ይህ ግዙፉ ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ መግባት በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የማዕድን ፍለጋ አሻራ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰፋ ስልታዊ እርምጃ እንደሆነ ታምኖበታል።

አስካሪ ሜታልስ በአውስትራሊያ የወርቅ እና መዳብ ማዕድናት ማውጣት ስራ ላይ እንዲሁም በናሚቢያ የሊቲየም ማዕድን ፕሮጀክቶች አሉት።

ከዚህ በተጨማሪም ባትሪዎችን ለዓለም አቀፍ ገበያዎች በማቅረብም ትሩ ልምድ ያለው ኩባንያም ነው።

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ማዕድናት ውስጥ አንዱ የሆነው ወርቅ ህገ ወጥ ንግድ የታሰበውን ያህል ገቢ ማግኘት ሳትችል ቆይታለች።

በዘንድሮው ዓመት በተደረገ ጥብቅ ቁጥጥር ወደ ውጭ ገበያ የሚላከው ወርቅ መጠን የጨመረ ሲሆን በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *