አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል።
አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አስታውቋል።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ“ ብሏል።
ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል።
በለንደን ማራቶን ውድድር አንደኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ 55 ሺህ ዶላር ሁለተኛ 33 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 22 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ የሆነው ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል ።
ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የአሜሪካው አለምአቀፍ የስፓርት ቻናል (ኢኤስፒኤን) ቀነኒሳ በቀለን የ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ አትሌት ነው ሲል መምረጡ ይታወሳል፡፡
የስፖርት ቻናሉ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ሌላኛዋ ኢትዮጵያት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ ያላቸውን የአፍሪካ ስፓርተኞች ይፋ አድርጓል።
አትሌት ቀነኒሳ በ2000ዎቹ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ሩጫዎች የበላይነት በመያዝ እስከ 2020 ድረስ የሁለቱም ርቀቶች ሪከርዶች በእሱ እጅ ነበሩ።
ቀነኒሳ በቀለ 3 ወርቅ በኦሎምፒክ ፣ 5 ወርቅ በአለም ሻምፒዮን ሽፕ፣ 11 ወርቅ በሀገር አቋሯጭ ውድድሮች ላይ መሰብሰባ የቻለ አትሌት ነው። ከዚህ በተጨማሪም ቀነኒሳ በቀለ ሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶንን ማሸነፍ ችሏል።