ኢትዮጵያ ለ10 ዓመት የሚያገለግል አዲስ ፓስፖርት ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ አራት አይነት ፓስፖርቶችን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ፓስፖርቶችን ይፋ አድርጓል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ይፋ የተደረጉት ፓስፖርቶች አራት አይነት ሲሆኑ ከመደበኛ ፓስፖርት በተጨማሪ የዲፕሎማት፣ ውጭ ሀገራት እና የአገልግሎት ፓስፖርቶችም ይገኙበታል።

ፓስፖርቶቹ በጃፓኑ ቶፓን የደህንነት ኩባንያ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ ትብብር ስለመመረቱም ተገልጿል።

10 ዓመት እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራው ይህ ፓስፖርት በአዲስ አበባ በሚገኘው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተመረተ ነው።

የፓስፖርቱ አገልግሎት ጊዜ 10 ዓመት መደረግ የዜጎችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት እንደሚቆጥብ ተገልጿል።

ይህ በዚህ እንዳለም በፓስፖርቱ ውስጥ ገጾች ላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታዎች የሚያጎለብቱ እና ታሪካዊ ቅርጾችን ይዟልም ተብሏል።

እንዲሁም ፓስፖርቱ የማይክሮ ችፕስ የተገጠመለት መሆኑ ሀሰተኛ ፓስፖርቶችን በቀላሉ መለየት እንዲቻል ተደርጎ ስለመሰራቱም በመድረኩ ላይ ተጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪም ፓስፖርቱ የግለሰቡን መረጃና የጣት ዐሻራ የያዘ እንደሆነም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ካሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ተቋም ከተገልጋዮች ቅሬታ ከሚበዛበት መካከል አንዱ ነው።

ዜጎች ፓስፖርት በወቅቱ ካለማግኘታቸው ባለፈ ለህገወጥ ስደት፣ ገንዘብ ብዝበዛ እና ለሌሎች እንግልቶች እንደሚዳረጉ ሲናገሩ ይደመጣል።

የኢምግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት በበኩሉ ለፓስፖርት ፈላጊ ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በየጊዜ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግሯል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *