አቶ ካሳሁን ፎሎ በድጋሚ የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡

(ኢሠማኮ) በአዲስ አበባ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኮንፌዴሬሽኑን በቀጣዮቹ 5 ዓመታት አመራሮችን መርጧል፡፡

በዚህም ላለፉት ዓመታት ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋ፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ አቶ ድሪብሳ ለገሰ እና አቶ አብዱልሐኪም ሙሰማ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ እንደመረጠም ሰምተናል፡፡

አቶ ካሳሁን ከምርጫው በኋላ ባደረጉት ንግግር በሀላፊነት የሚቀጥሉት ለመጨረሻ ጊዜ እንደሆነ በጉባኤው ላይ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም መንግሥት ለሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን በድጋሚ ጠይቀዋል።

ካሳሁን፣ መንግሥት ሠራተኞች በሚከፍሉት የደመወዝ ገቢ ግብር ላይ ቅናሽ እንዲያደርግ ኢሠማኮ በተደጋጋሚ ሲጠይቀው ለነበረው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥም አሳስበዋል።

በዓለማቀፍና የአገር ውስጥ ችግሮች ሳቢያ ሠራተኞች የኑሮ ውድነቱን ሊቋቋሙት ከሚችሉት በላይ እንደኾነባቸው የጠቀሱት አቶ ካሳሁን፣ በተለይ መንግሥት በቅርቡ ያደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በደመወዝ የሚተዳደሩ ሠራተኞችን የኑሮ ኹኔታ ወደከፋ ደረጃ እንዳሸጋገረው ገልጸዋል።

ኢሠማኮ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ በአገሪቱ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የሚወስን ቦርድ እንዲቋቋም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መመሪያ የሰጡት ባለፈው ዓመት ነበር።

ኾኖም ገንዘብ ሚንስቴር በቅርቡ አስጠናው በተባለ ጥናት፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን መወሰን በርካታ ሠራተኞችን ሥራ አጥ ያደርጋል የሚል ድምዳሜ ላይ እንደረሰ አንዳንድ የዜና ምንጮች ዘግበው ነበር።

ካሳሁን በዚኹ ንግግራቸው፣ በአገሪቱ በትጥቅ ግጭቶች ተሳታፊ የኾኑ ኹሉም ወገኖች ወደ ሠላማዊ መንገድ እንዲመለሱም ጥሪ አድርገዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *