የፌደራል መንግስት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ዓመታዊ በጀት አስጸደቀ

የዘንድሮ ዓመታዊ በጀት ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር አድጓል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መንግሥት ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የተጋነነ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ከስድስት ወር በፊት ለተያዘው በጀት ዓመት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጸድቆ ነበር፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እንዲጸድቅለት በቀረበለት ጥያቄ ዙሪያ መክረዋል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ለዕዳ ክፍያ፣  ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ እንዲሆን መታሰቡን  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጂጌ ተናግረዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት መንግስት ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የተጋነነ ነው ሲሉ ተቃውሞ ቅርበዋል፡፡

ይሁንና ከ2017 አስከ 2021 ድረስ የተነደፈውን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊስካል ፖሊሲ ማዕቀፍ ማሻሽያ ተከትሎ ከታክስና ከወጪ ፋይናንስ የሚገኘውን ገቢ በመጨመሩ ለመደበኛ ስራዎች እና የወጪ አሽፋፋን ለማስተካከል ተጨማሪ በጀት ማጽደቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

በዚህም ለበጀት ዓመቱ ያስፈለገው ተጨማሪ በጀት 582 ቢሊዮን ብር ነው ብለዋል፡፡

ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊዮን እና ለወጪ አሸፋፈን 119 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርበዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ተጨማሪ በጀቱ ህዝቡን  ለተጨማሪ ግብር የሚዳርግ እና የሚያማርር ሊሆን ይችላል ሲሉም ተችተዋል፡፡

በመጨረሻም የምክር ቤቱ አባላት የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀትን አጽድቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *