የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

መንግስት 550 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አዘጋጅቷል

ከሁለት ወር በፊት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጽድቆ የነበረው የፌደራል መንግስት ግማሽ ትሪሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳሉት የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ  ተናግረዋል።

መንገስት ካቀረበው 550 ቢሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ “ለማኅበራዊ ድጋፍ ” የሚውል ነው የተባለ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለሰራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣ ለመድሃኒት ድጎማ፣ ለለነዳጅ ድጎማ እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ድጎማ እንደሚውል ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የፌደራል መንግስት የበጀት ማስተካከያ ያደረገው ከዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ በብድር እና እርዳታ ማግኘቱን ተከትሎ ነው፡፡

እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ተቋማት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረትየኢትዮጵያ መገበያያ ገንዘብ የሆነው ብር  ከውጭ ሀገራት ምንዛሬ ተመን ጋር ያለው የመግዛት አቅም በመዳከሙ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ የ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡

የዓለም ባንክ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባሳለፍነው ሳምንት ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል።

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት 1 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ እርዳታ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ማራዘሚያ እንዲሁም 320 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር በሚል ለኢትዮጵያ የሚደረግ ድጋፍ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ እንዲሁም 6 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂ ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደምታገኝ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የውጪ ንግድን ለማሳደግ በሚል የብርን የመግዛት አቅምን በእጥፍ እና ከዛ በላይ ያዳከመች ሲሆን አሁን ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100 ብር እና ከዛ በላይ እየተመነዘረ ይገኛል፡፡

By New admin

One thought on “የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

  • Thank you I have just been searching for information approximately this topic for a while and yours is the best I have found out so far However what in regards to the bottom line Are you certain concerning the supply.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *