ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በፓርላማ በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡
የናይል ተፋሰስ አባል የሆኑ 11 ሀገራት በኡጋንዳ ኢንተቤ ባደረጉት ስምምነት የናይል ወንዝን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ስምምነት ነው፡፡
ስምምነቱ ከ11 የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ስድስት ሀገራት በፓርላማ ካጸደቁ ቋሚ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት ይችላል ተብሏል፡፡
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እንደገለጹት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ከተፈረመ ቆይቷል፡፡ አምስት ሀገራት በፓርላማቸው አጽድቀው ነበር፡፡
የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ለመመስረት የሚጠበቀው ስድስተኛ ሀገር በፓርላማ እስኪያጸድቅ ድረስ ነበር፤ ደቡብ ሱዳን አጸድቃለች ብለዋል፡፡
ስድስት ሀገራት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ማጽደቃቸው ፋይዳው ከፍተኛ ነው ያሉት አምባሳደሩ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት በሙሉ በሰነዱ ይገዛሉ፡፡ በሐምሌ አንድ ቀን 2016 ዓ.ም የደቡብ ሱዳን በፓርላማ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡
የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ለማጸደቅ ሂደቱ በጣም ከባድ ነበር ያሉት አምባሳደር ነቢል፤ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለፉት ሶስት አመታት ብዙ ትግል አድርጓል፡፡ የደቡብ ሱዳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከአምስት አመት በፊት ያጸደቀው ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ገልጸዋል፡፡
በፓርላማ ውስጥ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር የተገኘ ውጤት ነው፡፡ የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት በመሆኑ የሰላም ስምምነቱን የፈረሙ ፓርቲዎችን በሙሉ በማነጋገር የመጣ ነው ብለዋል፡፡ መፈረማቸው ለደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጽድቃለች ያሉት አምባሰደሩ፤ በቅርቡ የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ይፈርማሉ፡፡ በመቀጠልም ሰነዱን ለአፍሪካ ህብረት በመላክ ሕጋዊ ሰነድነቱ ይረጋገጣል፡፡
ከደቡብ ሱዳን በፊት የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፈርመዋል፤ይሁንና ወሳኙ ስድስተኛ ሀገር መፈረም በመሆኑ ደቡብ ሱዳን መፈረሟ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ጉዳዩን የኢትዮጵያ መንግስት የቅርብ ክትትል ያደረገበት በመሆኑ የተሳካ መሆን ችሏል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን መፈረሟ ለኢትዮጵያ ያላትን አጋርነት ያሳያል፡፡ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ነጻነት ከፍተኛ መስዋትነት ከፍላለች፡፡ ደቡብ ሱዳንም አጠቃላይ ለተፋሰሱ ሀገር በተለይ ለላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ያላትን አጋርነት ያረጋገጠችበት ነበር ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋዳንዳ፣ ብሩንዲና ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማእቀፍን ያጸደቁ ሀገራት ናቸው፡፡
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት እአአ 2006 የተዘጋጀ ሲሆን የናይል ተፋሰስ አገራት የውሃ ሀብቶችን በትብብር ማልማትና ማስተዳደር የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ያስቀመጠ ነው፡፡
የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ (NBI) የሽግግር ማእቀፍ ሆኖ በዘጠኝ መስራች አባል ሀገራት የጋራ ራእይ የተመሰረተና ቋሚ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን እስከሚመሰረት የሽሽግር ማእቀፍ ሆኖ እንዲያገልገል ታስቦ መቋቋሙ ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስምምነቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማጽደቋ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ነው ብለዋል፡፡
“የደቡብ ሱዳን ስምምነቱን ተቀብላ ማፅደቅ የናይል ተፋሰስ ኮሚሽንን በማቋቋም የህዝባችንን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መነቃቃትን ይፈጥራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መልዕክታቸው።
ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን በህዝበ ውሳኔ ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ስትሆን ከሶስት ወራት በፊትም የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በአዲስ አበባ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ወቅትም ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ738 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የብድር ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን የሚያገናኝ 220 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ እንደሚከናወንበት የተገለጸ ሲሆን የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት ብድሩን አጽደቋል፡፡
I was just as captivated by your creations as I was. The drawing you’ve created is stunning, and the writing you’ve done is sophisticated. However, your remarks indicate that you are worried about the possibility of engaging in something that may be seen as dubious. I’ll be able to resolve this quickly.