ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ የቡና ንግድ በታሪክ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቷን አስታውቃለች፡፡

ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ በዘንድሮው በጀት አመት ከአንድ ነጥብ 4 ቢሊዮን  ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በ2016 በጀት አመት ከቡና ሽያጭ በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ የሆነ ውጤት አስመዝግባለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት 298 ሺህ 500  ቶን ቡና ለውጪ ገበያ አቅርባ 1 ነጥብ 43 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች።

ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠንም ሆነ በገቢ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ  ጨምረው ገልፀዋል።

የተላከው የቡና መጠን በ20 በመቶ እንዲሁም በዋጋ ደረጃም በ7 ነጥብ  5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 240 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ሀገራት ልካ አንድ ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን ባለስልጣኑ በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡

እንዲሁም በ2021/22 በጀት ዓመት ደግሞ 302 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ 1 ነጥብ 34 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *