አፍሪካ በአለምአቀፍ የብሮድካስት መዝናኛ ኢንደስትሪ ውስጥ ያላትን ቦታ እንዲረጋገጥ ባለፉት 50 ዓመታት የተሰሩ እንቅስቃሲዎች ላይ ትኩረቱን ያደረግውና በተለይም የቀድሞ የመልቲቾይስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ለረጅመ ጊዜ ያገለገሉት ኖሎ ሌተሌ አስተዋዎ የሚቃኝው አዲስ ዘጋቢ ፊልም “አዎ ለማይቻለው፣ የኖሎ ሌተሌ ታሪከ ” በሚል ርዕስ ተዘጋጀቶ ለእይታ ሊበቃ ነው፡፡
ዘጋቢ ፊልሙ በመላው አፍሪካ ነፃነት ለማግኘት የሚደረጉ እንቅስቃሲዎች በተንሰራፋበት ወቅት በታዳጊ ዕድሚ ላይ የነበሩት ኖሎ አህጉሪቱ የራሷ የሆነ ድምጽ እንዲኖራት የነበራቸውን ራዕይ እንዴት እንደቀረፁት ፣ ይህንንም ራዕይ እውን ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውነ ያላሰለሰ ጥረት እና ረጅም ጉዞ በጥልቀት የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡
በሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪከ ምህንድስና ትምህርት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በዚያን ጊዜ የአፓርታይድ ስርዓት የምትከተለው ደቡብ አፍሪካ እንደ አንድ ጥቁር የሃገሪቱ ዜጋ በሙያው ስራ ባለማግኘት የተጀመረው ጉዞ ኖሎ ሌተሌን ወደ ሌሴቶ ናሽናል ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ እንዲያመራና የትንሽ ራዲዮ ጣቢያ እንዲቀላቀል ያደረገው ሲሆን የዚችን አነስተኛ የራዲዮ ጣቢያ ቆይታ ተከትሎ በሌሴቶ ክተማ መጀመሪያ የሆነውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ምስረታ ትልቅ ሚና ተጫወተ።
በመቀጠልም ወደ ኤም-ኔት ያመራው ኖሎ ዲኤስቲቪን ዛሬ ባለበት ደረጃ የማብቃት ከባድ ሀላፊነት የተቀበለበት ወቅት ሲሆን የሀገሪቱ የፖለቲካ አስቸጋሪ ነባራዊ ሁኒታ ሳይገድበው የመልቲቾይስን ወደ ቀሪው አፍሪካ ሀገራት መስፋፋት ስራ በውጢታማነት ያሳካ ሲሆን ወደ ደቡበ አፍሪካ በመመለስ የመልቲቾይስ ዋና ስራ አስፈሚነትን እስከሚቀበልበት ጊዚ ደረሰም በጋና መቀመጫው በማድረግ የምዕራብ አፍሪካ ቀጠና ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ አገልግሏል።
እንደ ኤሮፓዊያን አቆጣጠር 1999 የመልቲቾይስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈሚነት በመሆን መሾሙት ኖሎ ሌተሌ በዚህ ሀላፊነታቸውን እስከ 2010 እኤአ ድረስ የቆዩ ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም ለ11 ዓመታት የመልቲቾይስ ደቡበ አፍሪካ ሆልዲንግስ ቦርድ አስፈፃሚ ሆነው አገልግግለዋል፡፡ የመልቲቾይስ ግሩፕ ከናስፕር ጋር ተለያይቶ የጆሀንስፐርግ ካፒታል ገበያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ
በመልቲቾይስ ቆይታቸው የተለያዩ የሀላፊነት ሚናዎች ላይ የሰሩት ኖሎ ሌተሌ ለአፍሪካ ሚዲያ ዕድገት ላበረከቸው ስራዎች የላይፍ ታይም አፍሪካ አቺቭመንት ፕራይዝ(Lifetime Africa Achievement Prize)፣ የናስፐርስ ፊል ዊበር ሽልማት (Naspers Phil Weber Award) የጥቁር ንግድ ሥራ አስፈፃሚ ክበብ ሊቀመንበር ሽልማት (Black Business Executive Circle Chairman’s Award)ን ጭምሮ የተለያዩ አሀጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ተበርከተውለተታል፡፡
ከአዲስ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ሌቴ እንዳሉት “አፍሪካን ከአለም ጋር በማገናኘት እና ለአህጉሪቱ ድምጽ በመስጠት በበኩሊ ላበረከትኩት ሚና ኩራት ይሰማኛል፣ የመልቲቾይስን ተደራሽነት በአፍሪካ ወደር የለሽ ነው እናም የአፍሪካ ህዝቦች የራሳቸንን ታሪኮች በራሳችን ቋንቋ እንዲናገር እድል ሰቶናል። ኢንዱስትሪዎችን አሳድገናል፣ ሥራ ፈጠርን እና ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ትርጉም ያለው አስተዋፅዖ አበርክተናል – ከ35 ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ አነስተኛ ክፍያ የቲቪ ንግድን ስቀላቀል ያየሁትን ራዕይ እውን ለማድረግ መቻላችን በጣም ደስታን የሚሰጠኝ ነገር ነው።”
ይህ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሐሙስ ሰኔ 6 እና 7 ፣2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡30 በአቦል ዱካ በተጨማሪም በኤምኔት ቻናል ተከታታዮች ሐሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት እንዲሁም በድጋሚ ሰኔ 7፣2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 የሚተላለፍ ይሆናል፡፡