የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚልየን ዶላር ያስገነባውን የመንገደኞች ማስተናገጃ አስመረቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ50 ሚልየን ዶላር ያስገነባውን አዲስ የአገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ዛሬ አስመረቀ።

በአየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የአገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከአገር ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ለሚደረጉ በረራዎች በዚህ ተርሚናል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አዲሱ የአገር ውስጥ ተርሚናል አየር መንገዱ የሚሰጠውን የአገር ውስጥ በረራ አቅም በዕጥፍ እንደሚያሳድገው አስታውቀዋል።

አየር መንገዱ 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት። የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አዲስ የተገነባው የአገር ውስጥ ተርሚናል የቱሪዝም ዘርፍ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

አየር መንገዱ ከሁለት ወራት በፊት በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የድጅታል ግብይት ማቀላጠፊያ መሰረት ልማቱን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከ63 በላይ ከተሞች በመብረር ላይ ሲሆን ይህም ከየትኛውም የዓለማችን አየር መንገዶች በላይ በአፍሪካ ሰማይ ላይ የሚበር አየር መንገድ አድርጎታል፡፡

በታህሳስ 1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ግብጽ ካይሮ አድርጓል፡፡

የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዱባዩ ኤርሾው ላይ ተገኝተው እንዳሉት አየር መንገዱ ከቦይንግ እና ኤርባስ 78 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማምተዋል፡፡

በ2022 ለ13 ሚሊዮን ዜጎች የበረራ መስተንግዶ የሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ አሁን ላይ 145 አውሮፕላኖች እንዳሉት የገለጹት ስራ አስፈጻሚው የ2035 እቅዱን ለማሳካትም ተጨማሪ 130 አውሮፕላኖችን መግዛት እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵ አየር መንገድ ከአንድ ወር በፊት 78 አውሮፕላኖችን ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ለመግዛት መስማቱ ይታወሳል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *