የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ያጋጠመውን የሲስተም ችግር አስመልክቶ እያደረገ ያለውን ስራ የደረሰበት ደረጃ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ፤ ችግሩ የት ጋር ነው ያጠመው የሚለው ላይ በባለሙያ ጥናት እየተደረገ ነው ገና አላለቀም ብለዋል።
በእለቱ ከተፈጠረው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ በተደረጉ ግብይች እና የገንዘብ ዝውወሮች ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በእለቱ ሊጠፋ የነበረ ወይም አንድ ሰው ገንዘብ ከአካውንቱ ገንዘብ ካስተላለፈ በኋላ ለተላከለትም ሰው ደርሶ ገንዘቡ ለላኪውም ተመለሶ የተተካ ወይም ሪቨርስ ያደረገ 801 ሚሊየን 417 ሺህ 800 ብር ነበር ብለዋል።
በእለቱ አጋጥሞ በነበረ የሲስተም ችግር በነበረበት መስመር ላይ 25 ሺህ 761 ደንበኞች ገብይት ፈጽመዋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዚሁ ሰዓት 238 ሺ 293 ጊዜ ግብይት ተፈጽሟል፤
ባለፈው 490 ሺህ ግብይት ተፈጽሞ እንደነበረ ማሳወቃቸውን ያስታወሱት አቶ አቤ ሳኖ፤ ከእነዚህ ችግር ባለበት መስመር የተፈጸመው ግይት 238 ሺ 293 እንደነበረ እና ሌሎቹ ግይቶች ችግር ባልነበረበት መስመር የተከናወኑ መሆናቸው አስታውቀዋል።
በእለቱ ተገቢ ያልሆነ ግብይት ወይም የገንዘብ ዝውውር የተፈጸመባቸው አካውንቶች 25 ሺህ 671 እንደሆነ ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ አንድ ደንበኛ በአማካይ ከ9 ጊዜ በላይ ግብይት ፈጽሟል ብለዋል።
በእለቱ አንድ ወይም ሁለት ግብይት የፈጸሙ ደንበኞች ጥርጣሬ ውስጥ እንዳልገቡ እና ያለ አግባብ የተወሰደ ገንዘብ ከሂሳባቸው ተቀናሽ ተደርጎ እንደሚመለስ መደረጉን ስታውቀዋል።
በዚህም በአካውንታቸው ላይ በቂ ገንዘብ ከነበራቸው 10 ሺህ ደንበኞች ላይ 44 ሚሊየን ብር ተመላሽ መደረጉን አስታውቀዋል።
ቀሪዎቹ 15 ሺሀ 8 ደንበኞች 207 ሺህ ግዜ ፈጽመዋል ያሉት አቶ አቤ፤ ይህም እያንዳንዱ በዚያ ሌሊት በአማካይ 14 ጊዜ ግብይት መፈጸሙን ያሳያልም ብለዋል።
ሂሳባቸው ላይ ካለው ብር ወስደው ከነበሩ 15 ሺሀ 8 ደንበኞች መካከል እስከ ትናንት ማታ ድረስ 372 ሚሊየን ድረስ ተመላሽ መደረጉንም አስታውቀዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 9 ሺህ 281 ሰዎች ሙሉ ሙሉ ያባቸው መክፈላቸውን እንዲሁም 5 ሸህ 160 በከፊል መመለሳቸውን እና ቀሪውን ለመክፈል ቃል መግታቸውን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት እስካሁን በድምሩ ሊጠፋ ከነበረው 800 ሚሊየን ብር ውሰስጥ 623 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም 78 በመቶ ያክል እንደሆነ አስታውቀዋል።
ቀረው 22 በመቶው ነው የማስለስ እና የማፈላለግ ስራ እየተከናወነ እንደሆነም ነው ፕሬዝዳነቱ የገለጹት።
በህገ ወጥ መንግድ ገንዘብ ከወሰዱት መካከል 567 ደንበኞች እንስሁን ጠፍዋልያሉት ፕሬዝዳቱ፤ ሙሉ አድራሻውን አልን እየፈለግናቸው ነው ብለዋል።
እነዚህ የጠፉ ደንበኞች የወሰዱት ገንዘብ 9.8 ሚሊየን ብር መሆኑን እና ከዚህም ውስጥ አንድ ሰው ያወጣው ትልቁ ገንዘብ 324 ሺህ ብር መሆኑንም ገልጸዋል
በተሰጣቸው እድል ገንዘብ ባልመለሱ ገንበኞች ላይ በቀጣይ ስለሚወሰድ እርምጃ በሰጡት ማብራሪያም፤
በባንኩ ቅርንጫፎች በያሉበት ስም ዝርዝራቸውን መለጠፍ እንዲሁም በባንኩ የማበራዊ ትስስር ገጾች ስማቸውን ማውጣት አንዱ ነው ብለዋል።
2ኛ እርምጃ ስማቸውን ከነፎቶዋቸው ጭምር በማውጣት ማሳወቅ ሲሆን በዚህም መመለስ ካቻሉ 3ኛ እርምጃ በህግ የመጠየቅ ይሆናል ብለዋል።
ባንኩ ያለአግባብ የተወሰደ ገንዘቡን አንድ ብር እንኳ ሳይቀር እንደሚያስልስም አቶ አቤ ቃል ገብተዋል።