በኢትዮጵያ የወንዴ የዘር ፍሬ መለገስ እንደማይቻል ተገለጸ

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ወንዶች የዘር ፍሬያቸውን ሴቶች ደግሞ እንቁላላቸውን መለገስ እንደሚቻል የሚያሳይ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል፡፡

ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው ከሆነ መሰረቱን በትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ከተማ ያደረገ አንድ የህክምና ተቋም የወንድ ዘር ፍሬያቸውን ለሚለግሱ 10 ሺህ ብር እንዲሁም እንቁላላቸውን ለሚለግሱ ሴቶች ደግሞ 30 ሺህ ብር እንደሚከፍል አስታውቋል፡፡

ይህ የህክምና ተቋም ልጅ መውለድ ያልቻሉ ሰዎችን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል ህክምና መጀመሩን እና ለዚህም የተለያዩ መስፈርቶችን አስቀምቷል፡፡

የጤና ሚኒስቴርን በጉዳዩ ዙሪያ እንዳለው ኢትዮጵያ ከበጎ ፈቃደኞች በተለገሱ የዘር ፍሬዎች አልያም እንቁላል ልጅ እንዲወለዱ የሚፈቅድ ህግ እንደሌላት አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ጸዳል ለአልዐይን እንዳሉት ኢትዮጵያ በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ያልቻሉ ባለትዳሮች ወይም ጥንዶች ከራሳቸው ብቻ በተገኘ የዘር ፍሬ ልጅ እንዲወልዱ የሚረዳ ህክምና በሀገር ውስጥ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውጪ ግን “ከበጎ ፈቃደኞች በተሰበሰበ የወንድ የዘር ፍሬ ወይም እንቁላል ልጆች እንዲወለዱ የሚፈቅድ አሰራር በሀገሪቱ የለም የለም” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህን የሚፈቅድ አሰራር ከሌላት በመቀሌ ከተማ የዘር ፍሬ እና እንቁላል ከበጎ ፈቃድ እሰበስባለሁ የሚለው ተቋም እንዴት ህጋዊ ተቋም ሊሆን ቻለ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ክልሎች ከጤና ጋር የተያያዙ የህክምና ፈቃዶችን የመስጠት ስልጣን አላቸው ነገር ግን የሚሰጡት ፈቃዶች ከሀገሪቱ የጤና ፖሊሲ እና አሰራር ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *