በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ

በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ባሳለፍነው ነሀሴ ለስድስት ወራት የታወጀው አስቸኳይ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት ተራዝሟል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በአማራ ክልል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት  አራዝሟል።

የምክር ቤቱ አባላት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ አደረጉት በተባለው ውይይት ከዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል፡፡

ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡

ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ህግ ማስከበር እንደማይችል እና የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡

ይህን ተከትሎም ከሀምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ነበር፡፡

በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ አዋጅ ምክንያት በማድረግ የአማራ ብሐየራዊ ንቅናቄ ፓርቲን ወክለው የምክር ቤቱ አባላት ከሆኑት ውስጥ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) እና ክርስቲያን ታደለ ያለ መከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መታሰራቸው ይታወሳል።

በአጠቃላይ ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ በባህር ዳር ፣ በጎንደር እና በኮምቦልቻ ከተሞች 706 ሰዎች መታሰራውን የፍትህ ሚኒስቴር ሚንስትር ጌዴዮን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን እንደማይደግፍ ገልጾ በአማራ ክልል የተጣለው አዋጅ ስድስት ወር ሳይሞላው እንደሚነሳ ከመንግስት ቃል እንደተገባለት መናገሩ ይታወሳል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዜጎችን የመንቀሳቀስ መብት እንደሚገድብ እና በክልሉ በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስራዎቹን ተዘዋውሮ መስራት እንዳልቻለም ህብረቱ አስታውቋል፡፡

አሜሪካ፣ አፍሪካ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ጦርነቶች እንዲቆሙ ፣ የድሮን ጥቃቶች እንዲቆሙ እና ልዩነቶቻቸውንም በንግግር እንዲፈቱ አሳስበው ነበር፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ በአማራ ክልል ንጹሃንን ከጥቃት በማይጋልጥ መልኩ ድሮን መጠቀማችንን እንቀጥላለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *