የሕዳሴው ግድብ አራተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ተጠናቀቀ

የግድቡ አራተኛ እና ና የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  “የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው፤  ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። ” በማለት የግድቡ የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በስራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ  እንኳን ደስ አላችሁ፤ ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል” ብለዋል።

ከ12 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታው 91 በመቶ ደርሷል ተብሏብ።

ኢትዮጵያዊያን በሚያዋጡት ገንዘብ እነ በመንግስት ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ ግድብ በ5ሺህ 200 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ ፕሮጀክት ነው።

የህዳሴው ግድብ ሁለት ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 350 ሜጋ ዋት ሀይል ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ሀይል በማመንጨት ላይ ይገኛል።

ግድቡ እስካሁን ከ180 በላይ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ቀሪ ግንባታውን ለማጠናቀቅ 60 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የህዳሴው ግድብ ከሁለት ዓመት በኋላ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ ከ40 ቢሊዮን በላይ ሜትር ኪዩብ ውሀ በግድቡ ውስጥ ይገኛል ተብሏል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *