በአዲስ አበባ ግብረሰዶም ይፈምባቸዋል የተባሉ መዝናኛ ቤቶች ታሸጉ

አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በከተማዋ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ፖሊስ እርምጃውን እየወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር እንደሆነ ገልጿል።

የተመሳሳይ ጾታ መዝናና ቤቶች ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ ወንጀሎች ይፈጸምባቸው ነበርም ተብላል።

ፖሊስ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ ጥቆማ እንደደረሰውም አስታውቋል ።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ ናቸው ብሏል።

ፖሊስ የተመሳሳይ ጾታ መዝናኛ ቤቶች ባለቤቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየታጣራባቸው እንደሆነም አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *