ኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ጠየቀች

ኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ግማሽ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

የቀድሞው ተዋጊዎችን የተሃድሶ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል ከ554 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ይህን የተናገሩት ኮሚሽኑ የቀድሞው ተዋጊዎችን መልሶ በዘላቂነት በማቋቋም ረገድ የመገናኛ ብዙሃን ሚናና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሃላፊ ገመዳ አለሚ በበኩላቸው ይህ  የገንዘብ መጠን በመነሻነት የታቀደ እንደነበረ የጠቀሱት ኮሚሽነሩ አሁን ላይ ግን ከተጠቀሰው ከፍ ማለቱን ተናግረዋል ።

በኢትዮጵያ 372 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዳሉ የተሀድሶ ማዕከል እና የሀገር መከላከያ ሚንስቴር በጋራ ያጠኑት ጥናት ያስረዳል።

የተመዘገበው አሐዝ ይህ ቢሆንም ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ፈትተው ወደ ህብረተሰቡ ቢቀላቀሉ እንኳ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ በዚሁ የውይይት መርሐ ግብር ተናግሯል።

በክልል ደረጃ ትጥቅ አንግበው ከመንግስት ጋር ሲዋጉ የነበሩ የልዩ ሀይል አባላት በሌላ ማዕቀፍ የሚታዩና ኮሚሽኑ እንደማይመለከተው ተገልጿል።

በአማራ ክልል ከትጥቅ መፍታት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው፣ የደህንነት ስጋት ባለመሆኑ ኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ከፍቶ ለመስራት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ኮሚሽነሩ አክለው ተናግረዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *