ኢትዮጵያ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 50 ቢሊዮን ብር በጀተች

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት የሀገር መከላከያ በጀት ወጪ ከ120 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል።

ለ2016 በጀት ዓመት ከቀረበው 801 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት በጀት ውስጥ ለመከላከያ ሚኒስቴር 50 ቢሊዮን ብር ሲመደብ ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ ተቋማትና አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙ ተገልጿል።

በ2015 በጀት ዓመት ውስጥ አጠቃላይ ከተበጀተው የመከላከያ ሚኒስቴር በጀት ድርሻ ከ12 ቢሊዮን በላይ ብር ደርሷል ተብሏል።

የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መፍትሔ ማግኘቱን ተከትሎ መከላከያ ሚኒስቴር ለ2016 በጀት ዓመት 50 ቢሊዮን ብር እንደተያዘለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበው የቀጣዩ ዓመት ረቂቅ በጀት ለመረዳት ተችሏል።

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው ረቃቅ በጀት ውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ መሠረተልማቶችን ወደነበሩበት ለመመለስ 20 ቢሊዮን ብር እንደተያዘም ሰነዱ ያመለክታል።

ለ2016 በጀት ዓመት ለክልሎች ድጎማ 214 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሁለት ዓመታት
በላይ ከፌዴራል መንግስት የበጀት ድጎማ ያለገኘው የትግራይ ክልል ለቀጣዩ በጀት ዓመት 12.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል።

ለክልሎች ድጎማ ከተያዘው በጀት ውስጥ እንደሁልጊዜው ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት ኦሮሚያ ፣ አማራና የደቡብ ክልሎች ሲሆኑ ፤ እንደቅደም ተከተላቸውም ብር 71.9 ቢሊዮን ፣ ብር 45.1 ቢሊዮን እና ብር 26.9 ቢሊዮን ተመድቦላቸዋል።

በተጨማሪም ፣ ሶማሌ 20.8 ክልል ቢሊዮን ብር፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝች ክልል 6.4 ቢሊዮን ብር፣ ሲዳማ ክልል 8.5 ቢሊዮን ብር ተደልድሎ በረቂቅ በጀቱ ቀርቧል፡፡

በተመሳሳይ ፤ ለአፋር ክልል 6.3 ቢሊዮን ብር፣ ለቤንሻንጉል ክልል 3.8 ቢሊዮን ብር፣ ለጋምቤላ ክልል 2.7 ቢሊዮን ብር፣ ለሃረሪ ህዝብ ክልል 1.5 ቢሊዮን ብር፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስታደዳር 5.2 ቢሊዮን ብር፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር 1.8 ቢሊዮን ብር ሆኖ በረቂቁ ተደልድሏል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *