ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው መታሰሩ ተገለጸ

Dawit Begashaw

በበርካታ የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት በጋዜጠኝነት ሙያ ያገለገለው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በጽጥታ ሀይሎች መታሰሩን የስራ ባልደረቦቹ ለኢትዮ ነጋሪ ተናግረዋል ።

ጋዜጠኛ ዳዊት ከሌሎች የስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን አራት ኪሎ ሚዲያ የተሰኘ የድጅታል ሚዲያ አቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኝ ነበር።

ጋዜጠኛው ለስራ ወደ ባህርዳር ከተማ ባቀናበት ወቅት ዛሬ ሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በጸጥታ ሀይሎች ተይዞ መወሰዱን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሙያ ባልደረቦቹ ነግረውናል።

ይሁንና የአማራ ክልልም ይሁን የፌደራል መንግሥት በጋዜጠኛ ዳዊት እስር ጉዳይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ኮለኔል ጌትነት ስለ ጋዜጠኛው እስር እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት፣ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ፣ በዓልዓይን እና ሌሎችን ሚዲያ ተቋማት በጋዜጠኝነት አገልግለዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *