የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የህወሀትን ከሽብር መዝገብ መሰረዝን ተቃወሙ

የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባት (ህወሀት) በትግራይ ክልል ያለውን የሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው።

ለሁለት ዓመት የዘለቀው ይህ ጦርነት ከ800 ሺህ በላይ ዜጎችን እና ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ የንብረት ውድመት አድርሷል።

በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል የተደረገው ይህ ጦርነት ባሳለፍነው ህዳር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።

ይህን ስምምነት ተከትሎም ጦርነቱ የቆመ ሲሆን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት በመመስረት ላይ ይገኛል።

እንዲሁም ህወሀት በግንቦት 2021 ላይ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ ነበር።

ይህ ህግ አውጪ ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ህወሀትን ከሽብር መዝገብ ላይ ሰርዟል።

የኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የህወሀት ከሽብር መዝገብ ላይ መሰረዙን ተችተዋል።

ፓርቲዎቹ ህወሀት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትጥቅ ሳይፈታ፣ በሀይል ከወረራቸው አካባቢዎች ሳይለቅ እና የህግ ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ ከሽብር መዝገብ ላይ መሰረዝ አልነበረበትም ብለዋል።

በጦርነቱ የተጎዱ ዜጎች ካሳ ስለሚያገኙበት ሁኔታ በግልጽ ውይይት ሳይደረግ እና የህግ የበላይነት ሳይረጋገጥ ምክር ቤቱ ህወሀትን ከሽብር መዝገብ ላይ መሰረዙ ታሪካዊ የህግ ጥሰት ፈጽማልም ብለዋል ፓርቲዎቹ።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *