ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር ሱፐር አፕ የተሰኘ አገልግሎት መስጫውን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ በፊት የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጥበት የነበረውን “ቴሌ ብር” መተግበሪያ አዘምኗል።

ዛሬ ይፋ ያደረገው ይህ የደንበኞች አገልግሎት ከዚህ በፊት በአገልግሎት ላይ ከነበሩት ሶስት ተጨማሪ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል።

አዲሶቹ አገልግሎቶች የታቀደ ክፍያ፣ ለቡድን ገንዘብ መላክ እና የእድል ጨዋታዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ናቸው።

የታቀደ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች የገንዘብ እና አየር ሰዓት ለመላክ እንዲሁም ወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀኑ ለመክፈል ቀድመው ማቀድ የሚያስችል እንደሆነ ተቋሙ አስታውቋል።

ሁለተኛው እና ዛሬ ይፋ የተደረገው የቴሌ ብር ተጨማሪ አገልግሎት ከአንድ በላይ ለሆኑ ተቀባዮች አስቀድመው በሚሞሉት መስፈርት መሰረት በአንዴ መላክ ያስችላልም ተብሏል።

ሶስተኛው አዲስ አገልግሎት ደግሞ የእድል ጨዋታ የሚባል ሲሆን አጠቃቀምን መሰረት ያደረገ የአጓጊ ሽልማቶች ባለቤት የሚያደርግ እንደሆነ በፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል።

ሙሉ ለሙሉ የመንግስት ንብረት የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም የ40 በመቶ ድርሻውን ለመሸጥ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል።

ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያን ቴሌኮም አገልግሎት የተቀላቀለው ሳፋሪ ኮም ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮም ዋነኛ ተፎካካሪ ሆኗል።

በኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሉ ሲሆን 60 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ደንበኞች አሉ።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *